Abstract:
የኢትዮጵያ የዓሳ ምርት በዋናነት የሚገኘው ከሀይቆች፣ወንዞች እና ግድቦች ዓሳን በማስገር
ከሚሰበሰብ ምርት ሲሆን ዓሳ ግብርና ገና ያልተነካ የግብርና ዘርፍ እንደሆነ ብዙዎች
ይስማሙበታሌ፡፡ ይህን እምቅ የአገራችን ሀብት ተጠቅሞ የዓሳ ግብርናውን ንዑስ ዘርፍ ለማሳደግ በዘርፉ
የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት፣ የቴክኖልጂ አቅርቦት ውስንነት እና ዘርፉን ሰማስተዋወቅ
አና አርሶ/አርብቶ አደሮችን እያገዙ የሚገኙ ባለሙያዎች በዘርፉ በቂ ዕውቀት ያላቸው
አለመሆን ዘርፉን ለማሳደግ ፈተናዎች ሆነው ቀጥለዋል፡፡ ይህ ማኑዋል በዚህ ረገድ
የሚያጋጥሙ ክፍተቶችን ለመሙላት ታስቦ ተዘጋጅቷል፡፡ ማኑዋሉ ከዓሳ ስነ-ህይወት
ጀምሮ የዓሳ ግብርና አሰራር አና ግብአቶቹን በመጨረሻም ዓሳን ለምግብነት አዘገጃጀት
ድረስ በ14 ክፍልች የተከፊተ ሲሆን ስለ ዓሳ ግብርና ፅንሰ ሀሳብ እና አተገባበር የተሻለ
ግንዛቤ እንደሚሰጥ የአዘጋጆቹ ሙለ እምነት ነው፡፡