Abstract:
በሚቀጥሉት ክፍሎች ለተሳካ የጥጥ ማብቀል ተግባር የሚሆኑት ልዩ ልዩ አስፈላጊ ነገሮች ሃሳብ ለቀረበባቸው አሠራሮች ምክንያት ከሆኑት ንግግሮች ጋር ቀርበዋል፡፡ እዚህ ላይ ዋና ዋናዎቹ ሃሳብ የቀረበባቸው ጉዳዮች ባጭር የተገለጹ ሲሆን ጉዳዩ በይበልጥ የተብራራበት የመጽሐፍ ገጽ ቁጥሮች ተጠቅሰዋል፡፡ ጥጥ በሀገሪቱ የእርሻ ታሪክ ውስጥ ረጅም ዕድሜ አለው፡፡ እንዲያውም ሊቃውንት የጥጥ ተክል በመጀመሪያ የተገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን ያምናሉ፡፡
ከጥቂት ዓመታት ወዲህ የጥጥ ተክል በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ሄዷል፡፡ ሆኖም በሀገር ውስጥ ያሉትን የጥጥ መዳመጫዎች ፍላጎት ሊያረካ አልቻለም፡፡ ለምሳሌ በ1959 ዓ.ም. 25ዐ ኩንታል፡፡ (ማለት 8ዐዐዐዐ ኩንታል ባዘቶ) የተመረተ ሲሆን መዳመጫዎቹ የሚችሉት ግን የዚህን እጥፍ ነበር፡፡ ባሁኑ ጊዜም ቢሆን የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ከሚፈልጉት ውስጥ የቀረበላቸው ባዘቶ ከ44 በመቶ አይበልጥም፡፡ እንዲሁም ለ1964 ዓ.ም. ከተወጠነው ውስጥ ባዘቶ ከ25 እስከ 3ዐ ከመቶ እንደሚያንስ ተገምቷል፡፡ ስለዚሀ በሀገር ውስጥ ያለውን የጥጥን ተፈላኒት አርክቶ በተጨማሪ ወደውጭም ለመላክ ከተፈለገ የጥጥን ተክል አሁን ካለው ይበልጥ ማስፋፋትን ይጠይቃል፡፡ እንግዲህ በደንብ ለማስፋፋት ስለሚቻልበት ዘዴ ሃሳብ ለመስጠትም ሆነ ስለቀረውም የጥጥ ተክል አስፈላጊውን መረጃ ለማቅረብ የሚመቸውን መንገድ ለማወቅ የእርሻ ምርምር ኢንስትቲዩት በሀገሪቱ የሚገኙትን ዋና ዋና የጥጥ ማብቀያ ስፍራወችን ሁሉ የሚጠቀልል ሰፋ ያለ ጥናት ጀምሯል፡፡ ውጤቱ እስኪታወቅ ድረስ ጊዜ መገስገሱ አልቀረም ቢሆንም ገና ለገና ጊዜው ያልፋል ብሎ በሆነው መንገድ ጥጥን አይተክሉም ሌላው የሰለጠነው ዓለም የሚጠቀምበትን ይህን የሚያዋጣውን በሳይንስ ጥናት የተገኘውን ዘዴ አኛም ልንጠቀምበት ይገባል፡፡