DSpace Repository

በቡና አመራረት የአረም ቁጥጥር፣ የፀረ-አረም መድሃኒቶች አያያዝና አጠቃቀም

Show simple item record

dc.contributor.author ታደሰ, እሸቱ
dc.date.accessioned 2018-10-03T19:10:22Z
dc.date.available 2018-10-03T19:10:22Z
dc.date.issued 2008
dc.identifier.citation ታደሰ እሸቱ፡፡ 2008፡፡ በቡና አመራረት የአረም ቁጥጥር፣ የፀረ-አረም መድሃኒቶች አያያዝና አጠቃቀም፡፡ የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት፡ አዲስ አበባ en_US
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/2645
dc.description.abstract አረሞች ከሰብሎች ጋር በሚሆኑበት ጊዜ ለሰብሎች ዕድገት አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ-ነገሮችን ውሃ ቦታና የፀሃይ ብርሃን በመሻማት ምርትንና ምርታማነትን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀነስ ያደርጋሉ፡፡ በጅማ ምርምር ማዕከል በተደረገ ጥናት በአረም ምክንያት የቡና ምርት ከ6ዐ እስከ 9ዐ በመቶ ሲቀንስ እንደሚችል ተረጋግጧል፡፡ በተጨማሪ በጌራ መለስተኛ ምርምር ማዕከል በተደረገ ጥናት በአረም ምክንያት የቡና ፍሬ ፈርጣማነት በከፍተኛ ሁኔታ ሊቀነስ እንደሚችል ተረጋግጧል፡፡ የሃገራችን ዋና ዋና ቡና አብቃይ አካባቢዎች ከፍተኛ ዝናብ በተራዘመ ጊዜ የሚያገኙ ስለሆነ ለቡናውም ዕድገት ሆነ ለአረሞች ዕድገት ተስማሚ ስለሆነ የቡና ሥራ ዓመቱን ሙሉ ከፍተኛ የሆነ የአረም ቁጥጥር የሚፈልግ በመሆኑ ለአረም ቁጥጥር የሚውለው በጀት ከፍተኛ ነው፡፡ በሰፋፊ የባለሃብቶች የቡና ማሳዎችም ሆነ በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ ተደጋጋሚ የአረም ምንጣሮና የመድኃኒት ርጭትት ይከናወናል፡፡ እነዚህን አረሞች ለመከላከል የተለያዩ የአረም መከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም ይቻላል፡፡ ከእነዚህ ዘዴዎች አንዱ ፀረ-አረም መድሃኒቶችን መጠቀም ነው፡፡ በጅማ ምርምር ማዕከል በተሰራ ጥናት በመሬት ውስጥ መራቢያና ምግብ ማከማቻ ሥራሥር ያላቸውን አረሞች በገጀራና በቁፋሮ ለመከላከል መሞከር አረሞቹን ከማራባት የዘለለ ጥቅም እንደሌለው ታውቋል፡፡ ፀረ-አረም መድሃኒቶችን ለመጠቀም መታወቅ ያለበት ጉዳይ ፀረ-አረሞች መርዛማ መሆናቸውንና በጥንቃቄ ካልተጠቀምንባቸው በሰው በእንስሳት በአጠቃላይ በማህበረሰቡ ውስጥ ከፍተኛ ቀውስ ሊያስከትሉ የሚችሉ መሆኑን ነው፡፡ en_US
dc.description.sponsorship የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት en_US
dc.language.iso other en_US
dc.publisher የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት en_US
dc.subject ቡና አመራረት፣ የአረም ቁጥጥር፣ የፀረ-አረም መድሃኒቶች፣ አያያዝና አጠቃቀም en_US
dc.title በቡና አመራረት የአረም ቁጥጥር፣ የፀረ-አረም መድሃኒቶች አያያዝና አጠቃቀም en_US
dc.type Working Paper en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search DSpace


Advanced Search

Browse

My Account