Abstract:
ተዛማች መጤ እፅዋት በኢትዮጵያ ብዝሀ-ሕይወትን በህዝቧ ኢኰኖሚያዊ ደህንነት ስጋት በመፍጠር ላይ ናቸው፡፡ ብዝሀ-ሕይወት መመናመን ከአካባቢ ውድመት ቀጥሎ በዓብይ ምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡ በአስጊነታቸው የሚታወቁት ጥቂት ተዛማች መጤ ዕፅዋት መካከል ፓርቴኒየም (Parthenium hysterophorus) የፕሮሶፒ ዛፍ (Prodopis juliflora) ቦጬ የውሃ አረም (Eichhornia Crassipes) የወፍ ቆሎ (Lantana camara) እና መራራ ፍሬ ያለው ቁልቀል (Euphorbia stricta) ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል አንዳንዶቹ በማወቅ ሌሎች ደግሞ በአጋጣሚ ወደ አገር ውስጥ የገቡ ናቸው፡፡
ተዛማች መጤ ዕፅዋት ቀደም ብሎ በተሰራጩባቸው አካባቢዎች የተደረጉ የተለያዩ የቅኝት ዘገባዎች ተጨባጭ እንደሚያስረዱት በአርሶ አደሩ ዕይታ በሰብል ምርት ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑ ታውቋል፡፡በተደረገው የምርት ቅነሳነትም ለምሳሌ ፓርቴኒየም በምስራቅ ኢትዮጵያ በማሽላ ሰብል ላይ ከ46-97% የማሳ ምርት እንደሚቀንስ ተዘግቧል፡፡ የፕሮሶፒስ ዛፍ ደግሞ በስምጥ ሸለቆ የአገሪቱ ክፍሎች በ7ዐዐዐዐዐ ሄ/ር የሚገመት የእርሻና የግጦሽ ቦታዎችን በመውረር ሌሎች እጸዋት እንዳይበቅሉና እንዳያድጉ ስለሚያደርግ የግጦሽ ሳርና የቅጠላቅጠል ዝርያዎች እንዲጠፉ በማድርግ የአካባቢውን አርብቶአደር ለችግር ዳርጓል፡፡