Abstract:
ለውዝ ሞቃትና ፀሐያማ አካባቢ ሊበቅል የሚችል ዓመታዊ የቅባት እህል ነው፡፡ ውሃ የማይቋጥርና አሸዋማ መሬት ለዕድገቱ በጣም ይስማማዋል፡፡ የለውዝ ሴቴና ወንዴ አበባ ከተገናኙ በኋላ ሐረግ መሰል ክፍሎች ከግንዱ ላይ ወደ መሬት ውስጥ ያድጋሉ፡፡ ፍሬ የሚያፈራውም የነዚህ ሐረግ መሰል ክፍሎች ከግንዱ ላይ ወደ መሬት ውስጥ ያድጋሉ፡፡ ፍሬ የሚያፈራውም የነዚህ ሐረግ መሰል ክፍሎች ጫፍ ወደ መሬት ውስጥ ከገባ በኋላ ነው፡፡ እነዚህ ሐረግ መሰል ክፍሎች አፈር ውስጥ መግባት ካልቻሉ ለውዝ ፍሬ ሊያፈራ አይችልም፡፡ ለውዝ በአገሪቱ ውስጥ የሚመረተው በእያንዳንዱ ገበሬ መጠነኛ ጥረት ነው፡፡ ሐረርጌ ኤርትራና ሸዋ ለውዝ በብዛት የሚመረትባቸው ክፍላተ ሀገራት ሲሆኑ ሌሎችም ተመሳሳይ የአየር ጠባይ አፈርሃ ከባሕር በላይ ከፍታ ያላቸው ክፍላተ ሀገራት ሊያመርቱ ይችላሉ የሚል ግምት አለ፡፡ አብዛኛው የለውዝ ዓይነት ከ12ዐ እስከ 15ዐ ቀናት ባለው ጊዜ ለመቆፈር ይደርሳል፡፡