Abstract:
ዓሣ ግብርና ዓሣን በሰው ሰራሽ የውሃ አካላት (ኩሬ ግድብ ወዘተ)እንዲሁም በተፈጥሮ የውሃ አካላት ላይ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችና (ተንሳፋፊ ቀፎ ጥምር ግብርና ወዘተ . . .) ተጨማሪ ግብአቶችን (መኖ የውሃውን ለምነት በማዳበር ወዘተ . . .) በመጠቀም ዓሣ የሚመረትበት የግብርና ዘርፍ ነው፡፡ ዓሣ ግብርና በቻይና እንደተጀመረና ባለፉት ጥቂት አስርት አመታት በአለም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣ የግብርና ዘርፍ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ (FAO, 2006)፡፡ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የባህር ወደብ የሌላት ሀገር እንደመሆኗ የዓሣ ምርቷ ባሏት ሀይቆች ወንዞችና ግድቦች ላይ ብቻ የተመሠረተ ነው፡፡