Abstract:
የችግኝ ጣቢያ ማለት ችግኞች በተለየ አንክብካቤና ጥበቃ የሚያድጉበት ሥፍራ ማለት ነው፡፡ የዛፍ ተከላ በሚታቀድበት ጊዜ በቅድሚያ የሚፈለገውን የችግኝ ዓይነትና ብዛት ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ በገበያም ሆነ ለአካባቢ ጥበቃ ወይም በጓሮ ደንን ማልማት ካስፈለገ ችግኞች በችግኝ ጣቢያ ውስጥ በቅድሚያ ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡
የዛፍ ተክሎች የሚለሙት እንደ ሌሎች ዓመታዊ ሰብሎች በቀጥታ በመስክ ላይ ዘራቸውን በመዝራት ሳየሆን በአብዛኛው ችግኞችን በመትከል ነው፡፡ ምክንያቱም በመስክ ላይ አዲስ የበቀሉ የዛፍ ችግኞች ከሌሎች ተክሎች ጋር ውሃና ሌሎች ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ተሻምተው ለማደግ ስለሚያቅታቸው የመፅደቅ አቅማቸው አነስተኛ ይሆናል፡፡ እንዲሁም ችግኞችን መስክ ላይ ከመትከል ይልቅ በችግኝ ጣቢያ ውስጥ ማዘጋጀት ወጭ ቆጣቢ ነው፡፡