Abstract:
በሥራ ላይ ያለ የእርሻ መሣሪያዎች አያያዝና አጠቃቀም
እንዱሁም ጥገናን በተመለከተ የተለያየ ዕውቀት በልምድና
በትምህርት መገኘቱ ይታወቃል፡፡ ሆኖም የእርሻ መሳሪያዎች
እንደመለያየታቸው መጠን አጠቃቀማቸውም ሊለያይ
ስለሚችል ተጠቃሚዎች ይህንን በመገንዘብ በአጠቃቀም
ጉድለት ወይንም በቸልተኝነት አደጋ ሣይፈጠር ሥራን
በአግባቡ ለማከናወን ይቻል ዘንድ ቅድመ ጥንቃቄ፤
የኦፕሬሽን፣ የጥገናና ማስተካከል መመሪያ፤ የአስተራረስ
ዘዴ፤ የማሳ ዝግጅት፤ የትራክተርና ኮምባይን ዋና ዋና
ክፍሎችና ሥራዎች፤ የኦፕሬሽን ዓይነት፤ የእጅ ምልክት
መገናኛ ዘዴ እንዲሁም የእርሻ መሣሪያ ስራ ከጨረሰ በኋላ
ሊደረግለት የሚገባውን እንክብካቤ በተመለከተ እና ጠቃሚ
ዕዝሎችን ያካተተ ለኦፕሬተሮችና ቴክኒሺያኖች ባላቸው
ዕውቀት ላይ በተጨማሪ ሊያግዙ የሚችሉ ነጥቦችን
በማሰባሰብ እንደሚከተለው ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡